🪜በደረጃ ኮንክሪት ስራ (Staircase Reinforcement & Formwork Preparation) ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች🏗️👷♂️
📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት እና ለደህንነት ቁጥጥር ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1️⃣ የፎርምወርክ እርጋታ እና ድጋፍ (Formwork & Scaffolding Support):
የደረጃው የእንጨት ፎርምወርክ ከስር የተደገፈበት ፕሮፕስ/ስካፎልዲንግ የኮንክሪቱን ክብደት እና የሰራተኞቹን ንዝረት መቋቋም የሚችል ጠንካራ መሆኑን ማረጋገጥ።
2️⃣ የብረት አሰራር እና ማደራረብ (Waist Slab & Landing Rebar Detail):
የደረጃው ዋና ብረቶች (Main Bars) እና የማቋረጫ ብረቶች (Distribution Bars) በዲዛይኑ መሠረት መታሰራቸውን፣ እንዲሁም ደረጃው ከወለሉ/ላንዲንግ (Landing) ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ ተገቢው የብረት መቆላለፍ (Development Length / Anchorage) መኖሩን ማረጋገጥ።
3️⃣ የኮንክሪት ከቨር (Concrete Cover Spacers):
በብረቱ እና በፎርምወርኩ መካከል ተገቢው የኮንክሪት ከቨር (ከ 2.5cm - 3cm) እንዲኖር የስፔሰር ፓድ (Concrete Spacer Blocks) ማድረግ፤ ይህ ካልሆነ ብረቱ ከስር ክፍት ሆኖ ለዛግ ይጋለጣል።
4️⃣ የደረጃዎች እኩልነት እና ጽዳት (Step Dimensions & Cleaning):
የራይዘር (Riser) እንጨቶች እኩል ከፍታ እና ስፋት መያዛቸውን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት በደረጃው ውስጥ ያሉ የእንጨት ፍቅፋቂዎችና ቆሻሻዎችን በደንብ ማፅዳት እና ፎርምወርኩን በውሃ ማረስ።
🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
@etconp
3August 30, 2026 1.8K 8