ለገርጂና ለጉለሌ ኢትዮ-ፓርነተሰ ት/ቤቶች ማህበረሰብ በሙሉ፡፡ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካለፉት አመታት እጅግ በተሻለ መልኩ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ስገልፅላችሁ ደስታዪ እጥፍ ድርብ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
ገርጂ ት/ቤት
· ለፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች- 175
· ፈተናውን ያለፉ- 174
· ውጤት ያልተገለፀለት- 1( በማጠራት ላይ የሚገኝ)
ጉለሌ ት/ቤት
· ለፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች- 86
· ፈተናውን ያለፉ- 86
ይህ ውጤት የታታሪዎቹ ተማሪዎቻችን እና ያለድካም እውቀታቸውን የሚያካፍሉት መምህራኖቻችን መሆኑ እሙን ነው፡፡ የወላጆች ድርሻ ምትክ አይገኝለትም፡፡ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባለት እንዲሁም የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ድርሻም ወሳኝ ነበር፡፡ ሁላችሁም ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ በኩባንያው ስም ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን፡፡ ገነነ ይልማ(ዋና ሥራአስኪያጅ)
August 26, 2026 5.9K 88