ለገርጂ፤ ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች እስካሁን ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ መደበኛ ተማሪዎች… — EPS (Ethio-Parents' school) — TG.ME

ለገርጂ፤ ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች እስካሁን ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ መደበኛ ተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ጊዜን ባሳወቅነው መሰረት አብዛኛው ወላጆች ያስመዘገቡ ቢሆንም ቁጥራቸው ውስን የሆኑ ወላጆች ምዝገባውን ያላከናወኑ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንድታስመዘግቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቦታው በአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ቢያዝ ሀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር
August 3, 2026 17.6K 63