ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
ትምህርት ቤታችን ለሚቀጥለው ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የቅድመ-ዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ፡ ይገኛል። በዚህም መሠረት ከጀማሪ 1 (KG 2) እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ደረጃዎች አዲስ ተማሪዎችን በመጠባበቂያ መዝገብ (Waiting List) ከሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የምናካሄድ መሆኑን እንገልፃለን።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
1. የአካዳሚክ ውጤት፦ የተማሪው/ዋ የዓመቱ አጠቃላይ አማካይ ውጤት 75% እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
2. የስነ-ምግባር ደረጃ፦ የተማሪው/ዋ ጠባይ (Conduct) በሪፖርት ካርዱ ላይ "A" መሆን አለበት ።
ማሳሰቢያ
• ለ 2019 የትምህርት ዘመን ከ9ኛ እስከ 12 ኛክፍል ምንም ዓይነት ቦታ የሌለን መሆኑን እንገልፃለን።
ትምህርት ቤቱ
Forwarded fromEPS Director
June 22, 2026 25.5K 157