የቀጠለ በሌላ መልኩ በስብከቶቻችን ላይ እንኳንንና የሌሎቹን አስተምሕሮ፣ልምምድ፣ዶግማ ለይቶ ማወቅ ይቅርና… — ሐመረ ኖኅ ሚዲያ — TG.ME

ሐመረ ኖኅ ሚዲያ#መናፍቅ ክፍል 1 አንዳንዴ በከበሩት አውደምሕረቶቻችን ላይ አንዳንዴም ባስ ሲል በንግስ በዓላት ላይ በሰባኪዎቻችን አንደበት የሚሰጡ ትምህርቶች መሰረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ይሁን ወይም የእቅበተ እምነት ትምህርት ወይስ የአንጻራዊ ትምህርተ ስነ መለኮት አንዱ በአንዱ ተደበላልቆ ይታያል። ለምሳሌ ስለ ጾም ጥቅም ፣የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ፣የቤተክርስቲያን አባቶች አስተምሕሮ ማስተማር ይበል የሚያስብል…
የቀጠለ
በሌላ መልኩ በስብከቶቻችን ላይ እንኳንንና የሌሎቹን አስተምሕሮ፣ልምምድ፣ዶግማ ለይቶ ማወቅ ይቅርና የቤተክርስቲያኒቷን እምነት፣አስተምሕሮ፣ልምምድ በትክክል ለይቶ የማያውቅ በዛ ያለ ምዕመን በመኖሩ የመናፍቃንን ሀሳብ፣አስተምሕሮ፣ልምምድ መጥቀስ ምዕመናንን ግራ ማጋባት ነው የሚሆነው።

በሌላ መልኩ መናፍቃን እንዲህ ይላሉ እንዲህ ያደርጋሩ በማለት መናገር ለመናፍቃኑ ነጻ ማስታወቂያ መስራት ነው የሚሆን

ነገ እንበልና አንድ ምዕመን ቢመነፍቅ
የመናፍቃንን ትምህርት ቀድመን በአውደምሕረት ስለነገርነው በቶሎ ትምህርቱ ጋር ይዋሃዳል።በመሆኑም መናፍቃኑ ወጪ ሳያወጡ ጉባኤ ሳይዘረጉ አሸነፉ ማለት አይደል

ሌላኛው አንዳንድ ጊዜ መናፍቃን እንደዚህ ይላሉ ተብሎ የሚነገረው እውነት ይሉት ይሆን የሚለው ራሱ አጠያያቂ ነው።

ሌሎች እንዲህ ይላሉ ለማለት ጥልቅ ነገረ ሃይማኖታዊ ጥናት ዳሰሳ ምርምር ይፈልጋል።
በመሆኑም እነ እንትና እንዲህ ይላሉ ማለት ከውጤቱ ኪሳራው ያመዝናል።

በመሆኑም ምን ይደረግ ከተባለ

መጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና የቤተክርስቲያንን ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መረዳት(ስነ ልቦና) ቃኝቶ ለምዕመናን ማስተማር

በመቀጠል ስለ ነ እንትና ማንሳት ከተፈለገ ጥልቅ በሆነ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመስርቶ ሳይቀጥፉ
አስተምሕሮአቸውን በሊቃወሰንቱ መካከል፣በመንፈሳዊ ትምህርትቤቶች ላይ መስጠት

አልያም በአውደምሕረት እነ እንትና እንዲህ ይላሉ ተብሎ አንጠልጥሎ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ከሐዋርያነ አበው ትምህርት አንጻር በመገምገም ስህተት መሆኑን በግልጽ ቋንቋ ለመዕመኑ ማሳየት ካልሆነ ግን አለማንሳቱ ይመረጣል።

ዲያቆን የኋላሸት

21/10/2018 ዓ.ም
ቢሾፍቱ(ደብረዘይት)
❤1
June 28, 2026 1.1K 2