የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የ70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠች የጌጃ ቃለ… — የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC — TG.ME

የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የ70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠች

የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ያከናወነችውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚዘክር የ70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች።

በዓሉ በ1ኛ ሳሙኤል 7፥12 “አቤንኤዘር” እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን፥ በበዓሉ ላይ በርካታ የምስጋና፣ የጸሎት ፕሮግራሞች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።

ይህ ታላቅ ክብረ በዓል ከነሐሴ 3 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

በ1948 ዓ.ም.“መሠረተ ሕይወት” በሚል ስያሜ ጉዞዋን የጀመረችው ይህች ታሪካዊት ቤተክርስቲያን፥ ባለፉት ዓመታት ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ለማድረስ ባደረገችው ጥረት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ከ60 በላይ አዳዲስ አጥቢያዎችን በመትከል ረገድ ታላቅ ታሪክ መሥራቷ ተጠቅሷል።

ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ጎን ለጎን ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ ማኅበራዊ ሥራዎችን ስታከናውን የቆየች ሲሆን ከምሥረታዋ ጋር ተያይዞ የተቋቋመው የመጀመሪያው የመሠረተ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሠረተ ትምህርት ቤት አሁንም ድረስ ለአካባቢው ማኅበረሰብ በሥነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የቤተክርስቲያኗ መሪዎች እንደተናገሩት፤ ነሐሴ 23 በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ወንጌላውያን አማኞች በሙሉ የሚሳተፉበት ታላቅ የምስጋና እና ራዕይ የማጋራት መርሃ ግብር ይካሄዳል ብለዋል።

በተጨማሪም ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዝማሬ እና ወንጌል ማወጅ የእግር ጉዞ መርሃ ግብር ይከናወናል። ይህ ጉዞ ከቤተክርስቲያኑ ግቢ ተነስቶ በሞላ ማሩ እና በአብነት በበላ
❤10
August 19, 2026 2K 1 2