የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የታወቀች አንጋፋ ቤተ እምነት ናት በማለት ተናገሩ።
ነሐሴ8 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛ የካውንስል ስብሰባ አካሄዷል። በስብሰባዉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን በመልክታቸዉም የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በረጅም የአገልግሎት ዘመኗ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የታወቀች አንጋፋ ቤተ እምነት ናት። ለዛሬው ሁለንተናዊ እድገት የቀደሙ መሪዎች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነበር። ያሉት ጠቅላይ ፀሐፊዉ ዛሬም ቢሆን ከትውልድ፣ ከአገርና ከሁሉ በላይ ከእግዚአብሔር የተሰጣትን ታላቅ መለኮታዊ አደራ በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባታል። ብለዋል የዛሬዎቹ መሪዎች ትላንትን በማስታወስ፣ ዛሬን በታማኝነት በማገልገል እና ነገን መሠረት በሚጥል ራዕይ በመመልከት ዋናውን ነገር ዋና አድርገው መቀጠል አለባቸውም በማለት አክለዋል።
ለኢቫንጀሊካል ዜና ሩት ዋቅጅራ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ
14August 18, 2026 2.1K 2






