📢 ውድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (ኢ.ኤ.አ) ሠራተኞች፤
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የታዳሽ ኃይል ምርምር፣ ስርፀት እና ስልጠና ማዕከል ከተቋማችሁ ጋር በመተባበር በኢ.ኤ.አ ውስጥ ያለውን የሥርዓተ-ፆታ ጥቃት (GBV) እና ወሲባዊ ትንኮሳ (SH) መከላከያ ፖሊሲዎች እና አሠራሮች ውጤታማነት ለመገምገም ሰፊ ጥናት እያካሄደ ይገኛል።
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ተቋሙ ለሁሉም ሠራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሃዊ እና ምቹ የሥራ ቦታ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ነው።
📌 ስለ መጠይቁ ማወቅ ያለብዎት፦
የሚወስደው ጊዜ፦ ከ15 ደቂቃ አይበልጥም።
ሚስጥራዊነት፦ ምላሽዎ 100% ሚስጥራዊ ነው። መጠይቁ ስም-አልባ (Anonymous) በመሆኑ ማንነትዎ ወይም የግል መረጃዎ በፍጹም አይሰበሰብም፤ አይታወቅምም።
እባክዎን የእርስዎን እውነተኛ እና ጠቃሚ ዕይታ ለማካፈል ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦ https://forms.gle/BYNQFxdeh236F1Ad8
ለሚያደርጉት ቀና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን!










