ዲሲፕሊን እና ዓላማ! ሁለት ጓደኛሞች በየቀኑ ጠዋት እየተነሱ ሩጫ መሮጥ ፈለጉ፡፡ አንደኛው ለምን እንደሚሮጥ… — Dr. Eyob Mamo — TG.ME

ዲሲፕሊን እና ዓላማ!

ሁለት ጓደኛሞች በየቀኑ ጠዋት እየተነሱ ሩጫ መሮጥ ፈለጉ፡፡

አንደኛው ለምን እንደሚሮጥ ሲጠየቅ፣ “ሩጫ ጥሩ ስለሆነ” ሲል መለሰ፡፡

ሁለተኛው ሲጠየቅ ደግሞ፣ “የሚቀጥለውን አመት ታላቁ ሩጫ አሸናፊ ለመሆን” ብሎ መለሰ፡፡

ከሁለቱ በጥሩ ዲሲፕሊን ሩጫውን የመቀጠል አቅም ያለው የቱ ይመስላችኋል?

መልሳችሁ “ሁለተኛው” የሚል ከሆነ የዲሲፕሊን ዋነኛውን “ንጥረ-ነገር” አግኝታችሁታል፡፡

አንድን የጀመራችሁትን ነገር በዲሲፕልን ለመቀጠል የመታገል ሁኔታ ካለባችሁ ያንን ነገር ከአንድ ዓላማ እና ግብ ጋር አነካኩት፡፡

ዓላማ እና ግብ ያልታከለበትን ተግባር በዲሲፕሊን የመቀጠላችሁ ሁኔታ አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ዲሲፕሊን እና ዓላማ እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። ዓላማ አቅጣጫ ይሰጣል፤ ዲሲፕሊን ወደዚያ አቅጣጫ እንድንቀጥል ያደርጋል።

“ምን ማድረግ አለብኝ?” ብቻ ሳይሆን “ለምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለው ጥያቄ አስፈላጊ ነው።

አንድ ተግባር ከትልቅ ዓላማ ጋር ሲገናኝ፣ የዛሬ ትንሽ መስዋዕትነት ትርጉም ያገኛል።

አንድ ሰው መሮጥን ስለሚወድ ብቻ ሳይሆን፣ ለሚፈልገው ውጤት እየተዘጋጀ እንደሆነ ስለሚያውቅ ይቀጥላል። በተመሳሳይ ሁኔታ ለማዳበር የምንፈልገው ዲሲፕሊን መነሻው ጠንካራ ዓላማ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ዛሬ ለማዳበር የሚያታግላችሁን የዲሲፕሊን አይነት በሚገባ በመገምገም፣ ከምን አላማ ጋር ግንኙነት እንዳለው አጣሩና ሁለቱን አነካኳቸው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
https://t.me/Dreyob
❤33👍12😱1🤩1
September 4, 2026 3.3K 1 17