ትችቱን ረገብ አድርጉት!
በሰማችሁት፣ ባያችሁት እና ባነበባችሁት ነገር ሁሉ ላይ ግምታዊ ሃሳብ ሰጭነት፣ ትችት-ተኮር አስተያየትና አክራሪ አቋም ያዥነት ማንንም ከሚጎዳው በበለጠ ሁኔታ እናንተንው እንደሚጎዳችሁ ታውቃላችሁ?
ከእንደዚህ አይነቱ ልምምድ ጋር ተያይዞ የሚመጣው መዘዝ ብዙ ነው፡፡
በሰው ነገር ጥልቅ እያሉ ከመኖር የሚመጣ ዓላማ-ቢስ ኑሮ መኖር፣ ሌሎችን በማጣጣል ያደግን የመምሰል የውሸት ስሜት እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የአንድን ነገር የጀርባ ታሪክና አመጣጥ ሙሉ ለሙሉ በማታውቁት ሁኔታ ውስጥ እየገባችሁ ሃሳብ ሰጪነቱን ረገብ አድርጉትና እስቲ ዝም ብላችሁ ራሳችሁን ማሳደግ ላይና ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!
1. ከመናገር በፊት ቆም ብሎ ማሰብ
ሙሉ ታሪኩን አውቃለሁ? የምሰጠው ምላሽ በእውነት ላይ የተመሰረተ ነው ወይስ ግምት? ይህን ማሰብ ወይም መናገር በእርግጥ ያስፈልጋል? የምሰጠው አስተያየት ሰዎችን ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል?
2. ትኩረትን ከሌሎች ወደ ራስ መመለስ
ሌሎች ምን እያደረጉ እንደሆነ እና ምን እየተወራ በመከታተል ጊዜን ከማጥፋት ይልቅ፣ ራስን ለመገንባት መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡ ሌላ ሰው ላይ ከመፍረዳችን በፊት፣ “እኔ ራሴ ምን ማስተካከል ያለብኝ ነገር አለ?” ብለን እንጠይቅ።
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
https://t.me/Dreyob

47
11
8September 3, 2026 4.7K 1 12