"ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ከሞት
ያተረፈው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምር"
በአንድ ወቅት አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) ግድግዳ ላይ ስእል ለመሳል ረጅም መሰላል አቁመው ስራቸውን እየሰሩ ነበር፡፡
ተመስጠው እየተጠበቡ እያለ መሰላሉ ያንሸራትታቸውና መሬት ይወድቃሉ፡፡ አስቡት! የፒያሳውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ወለል፡፡ እዚያ ላይ ነው የወደቁት፡፡
እሳቸውም ሆኑ ሌሎች መትረፋቸውን አላመኑም ነበር፡፡ ግና አንዳች የህመም ስሜትም ሆነ ጉዳት ሳይገጥማቸው በጤና ሊገኙ ችለዋል፡፡
እሳቸውም ሆኑ በዙሪያቸው የነበሩ ሁሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምር መትረፋቸውን ነው የሚያምኑት፡፡ በተአምር ያተረፋቸውን ቤተክርስቲያንም ሲያገለግሉ ነው የኖሩት .....
ገና በ 15 ዓመታቸው በ 1940 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስ እና ትምህርት ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ተላኩ፡፡
ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በተለያዩ ግዛቶች በመዘዋወር የኢትዮጵያን ታሪክ እና ባህልና ወግን አጥንተዋል ።
ከዚህ በፊት በሐረር ከተማ ቆሞ የሚታየውን የልዑል ራስ መኮንን ሀውልት የቀረጹት እሳቸው ነበሩ ። አሁን ላይ በሚሳዝን ሁኔታ ሀውልታቸው እንዲፈርስ ተደርጓል ።
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ከታዋቂ ሥራዎቻቸው ከፊሎቹ:-
° በአዲስ አበባ በቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አዳራሽ መግቢያ የሚታየው በመቶ ሃምሳ ካሬ ሜትር ላይ የተሳለው ትልቅ የመስታወት ስዕል
° አዲስ አበባ በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ስዕሎች ፣ ሞዛይኮች
° አዲስአበባ አበባ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘውን የመጀመሪያውን የ’ዳግም ምጽዓት ፍርድ ስዕል
° በለንደን ‘ታወር ኦፍ ለንደን’ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ከብር እና ከእንጨት የተሠራ የመንበር መስቀል
° በሩሲያ ፣ አሜሪካ እና በሴኔጋል ኤግዚቢሽን ላይ የቀረበው "የመስቀል አበባ" ስዕል
° “እናት ኢትዮጵያ" (ከላይ ከፎቶው የምትመለከቱት)
° የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስል እና "ደመራ" ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ከዚህ ሁሉ ስራቸው በተጨማሪ ግን ጨረቃ ላይ ስማቸው የተፃፈላቸው ብቸኛው ጥቁር መሆናቸውና የሀገራችን ኢትዮጵያን ሠንደቅም አብረው ስላሰቀሉልን ልባችን በኩራት ይሞቃል።
አንጋፋው ሰአሊ በ80 አመታቸው ሚያዝያ 2/2004 ዓ.ም ነው ከእዚህ አለም ድካም ያረፉት። ሥርዓተ ቀብራቸውም ሚያዚያ 6/2004 ዓ.ም. ነበር በቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመው፡፡
"ስለ ኢትዮጵያ"
ክፉ አትይ ...!
ክፉ አትስማ ...!
ክፉ አትናገር ...!
ሊቀ ሊቃውንት ፣ የኪነ ጥበብ ምሑር ፣ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ።
ክብር ለጀግኖቻችን።
T.me/GhionMaleda
በውድነህ ክፍሌ| ግዮን ማለዳ











