የሞት ምስጢር እንዴት ይፈታል? የሞት ምስጢር እንዴት ይፈታል? አንድ ዝምተኛ አካልስ እንዴት ማስረጃን… — 𝖉𝖗. 𝖉𝖊𝖇𝖔𝖑 — TG.ME

የሞት ምስጢር እንዴት ይፈታል?

የሞት ምስጢር እንዴት ይፈታል? አንድ ዝምተኛ አካልስ እንዴት ማስረጃን ይናገራል? እውነት በሞት ጥላ ስር ተደብቆ ቢሆንስ?

MAC Ethiopia ከዶ/ር ተስፋዬ ገብረወልድ፣ የፎረንሲክ ሕክምናና ቶክሲኮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን «ዝምተኛው እማኝ» የተሰኘውን የፎረንሲክ ሕክምና ትሪለር መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው።

    «ዝምተኛው እማኝ»
በኢትዮጵያ በአይነቱና በይዘቱ የመጀመሪያ የሆነና ከእውነተኛ የፎረንሲክ(የአስክሬን ምርመራ) ግኝቶችና ከሕክምናዊ እውነታዎች ተነስቶ፣ የሞትን ምስጢር ወደ ሳይንስ፣ የሳይንስን ምርመራ ወደ ተደበቀው እውነት ፣ እውነታንም ወደ ሕያው ታሪክ የቀየረ ልዩ መጽሐፍ ነው። በፎረንሲክ ሕክምና፣ በወንጀል ምርመራና በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ መካከል አዲስ ድልድይ የፈጠረ፣ ከኢትዮጵያዊ የሙያ እውቀትና ከሥነ-ጽሑፋዊ ጥበብ የተወለደ ድንቅ ስራ ነው።

እውነተኛ ጉዳዮች፣ የተደበቁ ምስጢሮች፣ የማይተኛ እውነት እና አንድ ዝምተኛ እማኝ።

ይህ ታሪክ በቅርቡ ወደ አንባቢ ይደርሳል።

የዚህ ልዩና ታሪካዊ ስራ አካል መሆን ወይም ምርትና አገልግሎትዎን በዚህ ሁለገብ መጽሐፍ ማስተዋወቅ ከፈለጉ፣ በውስጥ መስመር ያናግሩን።

+251922401205
🔥34❤21👏3
August 24, 2026 5.3K 4