Defence Construction Enterprise: post #2162 — TG.ME

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  የችግኝ ተከላ  አካሂደዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕና የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራሮችና ሠራተኞች በ8ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤትና የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራሮችና ሠራተኞች በቢሾፍቱ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በጋራ በመገኘት አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ኃይለማሪያም፣ የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ተክሉ ፀጋዬና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራርና ሠራተኞች በዋና መሥሪያ ቤቱ እንዲሁም በተቋሙ በሚያከናውናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለአካባቢው የአየር ፀባይ ተስማሚ የሆኑና በረሃማነትን ለመከላከል የሚያግዙ የአትክልትና የፍራፍሬ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ተክለዋል።

የተቋማቱ አመራርና ሰራተኞች እንደገለጹት፣ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር፣ የደን ሽፋንን ለመጨመር፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። ዘገባው የክፍሎቹ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤2
August 3, 2026 1.7K