የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የማዳበሪያ አቅርቦት ሰንሰለትን ለማጠናከር የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ።… — Development Bank of Ethiopia (DBE) — TG.ME

የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የማዳበሪያ አቅርቦት ሰንሰለትን ለማጠናከር የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ።
የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የዓለም ባንክ ፣ የአውሮፓ ባንክን ጨምሮ የባለብዙ ወገን የልማት ባንኮች እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት።
ስምምነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ አቅርቦት ሰንሰለትን ለማጠናከር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተስፋ ተጥሎበታል።
በማዳበሪያ ምርት፣ በማቀነባበር፣ ማከማቸት እና ማጓጓዝ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ የፋይናንስ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ ባንኮቹ ከተስማሙባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የሚጠቀስ ነው።
በተለይም ለአነስተኛ አርሶ አደሮች እና ለግብርና ኢንተርፕራይዞች የማዳበሪያ፣ የፋይናንስ እና የገበያ እድሎችን በስፋት ለማመቻቸት የፋይናንስ ተቋማቱ ተስማምተዋል።
ይህ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ የሚፈጠሩ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለአነስተኛ አርሶ አደሮች ተስፋ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
👍4❤1👏1
September 1, 2026 1.1K