አፍሬክስም ባንክ ውጤታማ የፋይናንስ አፈጻጸም አስመዘገብኩ አለ። የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ… — Development Bank of Ethiopia (DBE) — TG.ME

አፍሬክስም ባንክ ውጤታማ  የፋይናንስ አፈጻጸም አስመዘገብኩ አለ።

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሬክስምባንክ) የ2026 የግማሽ ዓመት የንግድና የኢኮኖሚ ልማት ሥራ የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

እንደ ሪፖርቱ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 52.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። ውጤቱ የማበደር አቅምን በማስፋፋት የተገኘ ነው።

የባንኩ የተጣራ ብድርና የቅድመ ክፍያ መጠኑ 35.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

የአፍሬክስም ባንክ ባለአክሲዮኖች ፈንድ ከፈረንጆቹ 2025 መጨረሻ 8.4 ቢሊዮን ዶላር ወደ 8.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።

በተጨማሪም የተጣራ የወለድ ገቢ ከቀድሞው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ22 በመቶ አድጎ 1.0 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል።

ባንኩ በግማሽ ዓመቱ 534.7 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ሲያገኝ ከ2025 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ30 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

በጥቅሉ አፍሬክስም ባንክ በ2026 ግማሽ ዓመት ውጤታማ የፋይናንስ አፈጻጸም ማስመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሬክስምባንክ) በአፍሪካ ውስጥና ከባህር ማዶ አገራት ጋር የሚደረግን ንግድ ለማስተዋወቅና ፋይናንስ ለማድረግ የተቋቋመ የፓን-አፍሪካ ባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋም ነው።
#DBE
❤3👍1
August 31, 2026 1.2K