𝐂𝐨𝐧𝐬𝐭𝐫𝐮𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 & 𝐌𝐚𝐧𝐚𝐠𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭: post #216 — TG.ME

የውጪ ቀለም በውድ ዋጋ ገዝቼ ሞያተኛ ሥራውን ቢያበላሽብኝስ የሚል ስጋት ብዙ ጊዜ ከባለቤት ይነሳል ፡፡
🔴ይህን ሥጋት ለመቅረፍ እነዚህን 3 መሰረታዊ ነገሮች አድርጉ
👉1. የምታሰሩትን ሞያተኛ በጥንቃቄ ምረጡ ፡
⭕️ልምድ ያለው መሆኑን የሰራቸውን ሥራዎች በማየት አረጋግጡ
⭕️ስነምግባር ያለው መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ
⭕️የራሱን ብቻ ሳይሆን የእናንተንም ሃሳብ የሚቀበል መሆኑን ያረጋግጡ

👉2. Sample/ናሙና እንዲሰራላችሁ አድርጉ
⭕️ሙሉ ለሙሉ ወደሥራ ክመግባቱ በፊት ሳምፕል በትንሽ ቦታ/ግድግዳ ላይ ሙሉ ሄደቱን ሰርቶ የመጨረሻ ገጽታው ምን እንደሚመስል ለናንተ ማሳየት ይኖርበታል። ካልተመቻቹ እንዲቀይር ካልቻለ ደግሞ ሌላ ሙያተኛ ማምጣት ይኖርባችኋል።
👉3. ሥራውን የሚከታተልላችሁ ባለሙያ ያስፈልጋችኋል።
⭕️የሚሰራውን ሥራ እናንተ መከታተል ካልቻላችሁ ስለቀለም እውቀት ያለው ባለሙያ/ መሃንዲስ መድባችሁ እያንዳንዳንዱን ሂደት እንዲከታተልላችሁ ማድረግ ይኖርባችኋል።
🟠ቤታችሁን ቀለም ማስቀባት ካሰባችሁ በሳይት እንጂነር የሚመሩ ባለሙያዎችን ይዘን በሙያዊ ሥነምግባርና በከፍተኛ ጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ እንድንሰራላችሁ ከፈለጋችሁ በ0910734529 ይደዉሉልን
❤2
June 8, 2025 1.4K 2