𝐂𝐨𝐧𝐬𝐭𝐫𝐮𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 & 𝐌𝐚𝐧𝐚𝐠𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭: post #233 — TG.ME

በአዲስ አበባ
​በኮንስትራክሽን ማዕድን ሥራ ላይ
​የተሰማራችሁ አልሚዎችና ተቋራጮች!
​ሰኔ 2018
​የወጣውን አዲሱን መመሪያ
​ሰምታችኋል?
​ስራችሁ እንዳይስተጓጎል
​እነዚህን አራት ወሳኝ ነጥቦች
​በፍጥነት እወቁ!
​አንደኛ፡ የፈቃድ ዘመን ገደብ
​ለጥቁር ድንጋይ ማምረቻ ፈቃድ
​ቢበዛ እስከ አምስት ዓመት፤
​ለገረጋንቲ፣ ለአሸዋና ለነጭ ድንጋይ ደግሞ
​እስከ ሁለት ዓመት ብቻ ነው የሚሰጠው።
​በየዓመቱ መታደስም አለበት!
​ሁለተኛ፡ ክልክል ቀጠናዎች 🚫
​ከቤትዎ ወይም ከኮንስትራክሽን ሳይትዎ አጠገብ
​ማምረት አይችሉም!
​ከመኖሪያ መንደርና ከኢንዱስትሪ ፓርክ
​አምስት መቶ ሜትር፤
​ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር
​ሃያ አምስት ሜትር፤
​ከወንዝ ዳርቻ ደግሞ
​ሰላሳ ሜትር ክልል ውስጥ
​ማዕድን ማምረት ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው!
​ሦስተኛ፡ አዲስ ፈቃድ ለማውጣት 📋
​በአዲሱ አሰራር መሠረት
​ማመልከት ያለባችሁ በፖርታል ብቻ ነው!
​በሕጋዊ አማካሪ የተና
​የአዋጭነት ጥናት እና
​የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማቅረብ
​ግዴታችሁ ነው!
​ለደረሰ ጉዳት ማስተካከያ የሚሆን
​የፋይናንስ ዋስትናም
​በባንክ ማስገባት ይጠበቅባችኋል።
​አራተኛ፡ የድንጋይ መፍጫ ማሽኖች ⚙️
​የድንጋይ መፍጫ ማሽን
​ወይም ባቺንግ ፕላንት ለመትከል
​ፈቃድ የሚሰጠው፤
​የማዕድን ማምረት ፈቃድ ላለውና
​በካባው ውስጥ በቂ ቦታ ለሌለው
​ሰው ብቻ ነው!
​የማሽን መትከያ ፈቃዱም
​ከማምረቻ ፈቃዱ ጋር አብሮ ያበቃል።
191_የኮንስትራክሽን_ማዕድን_ፈቃድ_አፈጻጸም_መመሪያ_ቁጥር_191_2018.pdf283.2 KB · PDF
July 10, 2026 514 1