አዲስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ 🛢️📈 በነዳጅ ዋጋ ላይ የ25 ብር ጭማሪ ተደረገ።… — Construction Proxy — TG.ME

አዲስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ 🛢️📈

በነዳጅ ዋጋ ላይ የ25 ብር ጭማሪ ተደረገ።

አዲስ አበባ | ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ስራ ላይ የሚውል አዲስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል 📢📅

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ የዋጋ ማስተካከያው የተደረገው የዓለም የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀደም ብሎ በተላለፈው የዋጋ ግንባታ ለፈጻሸም ውሳኔ መሠረት መሆኑ ተገልጿል 🌍📊

በአዲሱ የዋጋ ማስተካከያ መሠረት አዲስ አበባ ከተማ የሚሸጡ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር፦🛒💰
1. ቤንዚን፦ 167.50 ብር
2. ኬሮሲን፦ 320.66 ብር
3. ነጭ ናፍጣ ፦ 180.46 ብር
4. ቀለል ያለ ጥቁር ናፍጣ ፦ 170.62 ብር
5. ከባድ ጥቁር ናፍጣ ፦ 167.37 ብር
6. የአውሮፕላን ነዳጅ፦ 319.76 ብር

መንግስት ይህ የዋጋ ማስተካከያ ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሱቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን፣ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም መላክዋል 🚗

©️የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

#fuel
❤41😭11😁3👏1
May 4, 2026 28.4K 119