ክፍል አንድ፡ ስለ አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ማወቅ ያለብዎት ወሳኝ ነጥቦች! * ማንኛውንም… — Construction Proxy — TG.ME

ክፍል አንድ፡ ስለ አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ማወቅ ያለብዎት ወሳኝ ነጥቦች!
*
ማንኛ
ውንም ግንባታ ከመጀመርዎ ወይም የጥገና ሥራ ከማከናወንዎ በፊት የአዋጁን ይዘት መረዳት ከሕግ ተጠያቂነት ከመታደጉም በላይ፣ ንብረትዎን ካልተገባ ብክነት ይጠብቃል። ለዛሬ የአዋጁን ተፈጻሚነት፣ የ"ህንፃ" ትርጉም እና የግንባታ ባለቤቶች ግዴታን እንደሚከተለው በዝርዝር አቅርበንላችኋል።

🏢 "ህንፃ" የሚለው ቃል ሰፊ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን የሚከተሉትን ግንባታዎች ያጠቃልላል፦
• ማንኛውም ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ ወይም ለሌላ አገልግሎት ታስቦ ከምድር በላይ ወይም በከርሰ-ምድር (Basement) የተገነባ ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ግንባታ፤
• እንደ አጥር፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች፣ የውሃና መብራት ዝርጋታዎች ያሉ ተያያዥ ሥራዎች፤
• በህንፃው ግቢ ውስጥ የሚሰሩ መንገዶች እና ለህንፃው አገልግሎት እንዲውሉ ተለይተው የተሰሩ ማናቸውም መሰረተ-ልማቶች።
📍 የአዋጁ ተፈጻሚነት ወሰን (አንቀጽ 3)
አዋጁ በማንና የት ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በአንቀጽ 3 ላይ በዝርዝር ተደንግጓል፦
• በከተሞች ውስጥ፦ 10,000 (አሥር ሺህ) እና ከዚያ በላይ ነዋሪዎች ባሏቸው ከተሞች በሚከናወኑ ግንባታዎች ሁሉ።
• ከከተማ ወሰን ውጭ፦ ለሕዝብ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎች (ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ወዘተ)፣ የኢንዱስትሪ ወይም የዘመናዊ እርሻ ተቋማት እና የሪል ስቴት ግንባታዎች።
• ለነባር ሕንፃዎች፦ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተገነቡ ሕንፃዎች ቢሆኑም፤ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ለማድረግ በሚደረግ ማሻሻያ እንዲሁም ለሕዝብ ደህንነትና ጤንነት አስጊ የሆኑ ሕንፃዎችን ለማስተካከል ወይም ለማፍረስ አዋጁ ተፈጻሚ ይሆናል።
@ConstructionProxy
የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ 1356.pdf1.4 MB · PDF
❤57😁1
April 30, 2026 34.2K 263