በአዲስ አበባ ሕንፃ አስገንቢዎች የሠራተኞችን ደኅንነት የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲመድቡ ሊደረግ ነው - ሪፖርተር… — Construction Proxy — TG.ME

በአዲስ አበባ ሕንፃ አስገንቢዎች የሠራተኞችን ደኅንነት የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲመድቡ ሊደረግ ነው
- ሪፖርተር -

በአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃ የሚያስገነቡ የሠራተኞችን ደኅንነትን የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲመድቡ እንደሚገደዱ፣ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አበበ እሸቱ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሥራ ላይ የሚያጋጥም ሞትን ለመከላከልና የግንባታ ደኅንነት መሠረታዊ አስፈላጊነትን ለማረጋገጥ የሕንፃ አስገንቢዎች በዘርፉ የሠለጠነ የደኅንነት ባለሙያ እንዲቀጥሩ ይገደዳሉ፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስችል መመርያ እንደሚወጣ ገልጸው፣ እያንዳንዱ የግንባታ ቦታ በሕግ ተደግፎ የደኅንነት ባለሙያ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
❤33👍18👏7🤯1
March 15, 2026 25.2K 29