እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሰላም ለሥጋኪ እግዚአብሔር ዘመሠጣ። ከመ ተሀሉ በህየ ለማህደረ ብርሃን በውስጣ። ወለተ ካህናት ማርያም ፈጻሚተ ቃላት የውጣ። አዕዳወ ፍቅርኪ በላዕሌየ ይሡጣ። እፍረተ መዓዛ ቅድወ ዘብዙኅ ሤጣ።
"እግዚአብሔር ወደ ላይ ለነጠቃት/ላረገችው ለሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። በብርሃን ማደሪያ ውስጥ ትኖር ዘንድ። የካህናት ልጅ ማርያም ሆይ፥ የብሉይ ኪዳንን ቃላት የምትፈጽሚ ነሽ። የፍቅርሽ እጆች በላዬ ላይ ይዘርጉ። መዓዛው እጅግ ያማረና ዋጋው ብዙ የሆነ ሽቶ ነሽ።"
ሐዋርያት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ዕረፍት በኋላ ከእነርሱ በመለየቷ ባዘኑበት ወቅት ወንጌላዊ ዮሐንስ በገነት ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ወደ ምድር ወረደ። ለሐዋርያትም መላእክት በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅጉን አዝነው በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ ነሐሴ ዐሥራ ስድስትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጇ ቀኝ ተቀምጣ፣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ፣ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት፡፡ እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን ባረከቻቸው፡፡ ጌታችን ሠራዔ ካሕን ቅዱስ እስጢፋኖስ ዲያቆን ሆነው ቀድሰው ሥጋውንና ደሙን አቀብሏቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ፡፡
ጌታችን አምላካችን በእመቤታችን አማላጅነት ይምረን ዘንድ ከበዓሏም በረከትን እናገኝ ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን! አሜን፡፡
የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ
Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube














