የመረጃ አያያዝን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
ነሐሴ 18 /2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በቁልፍ አፈፃፀም አመላካች (KPI) እና በዕቅድና ሪፖርት ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም (PRMIS) ከከተማ እስከ ወረዳ ተግባራዊ ለማድረግ ለባለሙያዎችና አመራሮች የቴክኖሎጂው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ እንደገለጹት የመረጃ አያያዝን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ እና በዘርፉ በቂ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች ግንዛቤ ማግኘት ለተቋሙ በቀጣይ ስራዎች ስኬት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልጸዋል ።
ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን፣ የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ እና የአሰራር ውጤታማነትን በዲጂታል ሲስተም ለመደገፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሰልጠናውን የሰጡት የፕላንና ልማት ቢሮ የአፈጻጸም ስራ አመራር ቡድን መሪ አለምወርቅ ዲኖ ገልጸዋል ።
ከወረቀት ነጻ የሆነ አሰራርን በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ቀላል እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ሲስተሙ የተጀመረዉን የዲጅታል አገልግሎት ለማጠናከርና ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጸዋል።
በስልጠናው የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ባለሙያዎችና አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡

















