ባለሥልጣኑ የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር አሰራሩን ለማዘመን የመገናኛ ሬዲዮ እና የመስክ ካሜራ ቴክኖሎጂ ግዢ ለመፈፀም ውይይት አካሄደ
15/12 /2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቱ ለማጠናከር የሚረዱ መሣሪያዎችና አስፈላጊ የደንብ ልብስ ለመግዛት ውይይት አካሄደ።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን የተቋሙ አላማዎችንና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ ግባቶች ግልጽ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የግዥ ስርዓት ለመዘርጋት ግባቶች እንደሚገዙ ገልጸዋል።
ተቋሙ የሀብት ብክነትን በማስወገድ፣ በጀትና ጊዜን በቁጠባ በመጠቀም ለአገልግሎት አሰጣጡ አስፈላጊ የሆኑ ዘመኑን መሠረት ያደረጉ ስራን የሚያቃልሉ እና የተሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት የሚረዲ ግባቶች ግዢ በወቅቱና በትክክለኛ ጥራት እንዲገዛ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አሰራሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማዘመን በዘንድሮ በጀት ዓመት የመገናኛ ሬዲዮ እና የካሜራ ቴክኖሎጂ ግዢ እንደሚፈፀም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።
የተቋሙን የግዢ ፍላጎት እቅድ ያቀረቡት የግዢ ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ እፀህይወት ፅጌ በተቋሙ የተጀመረው ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለማስቀጠልና ለማዘመን ከሁሉም የስራ ክፍል ፍላጎት መሰብሰቡን ገልፀዋል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
3
2August 24, 2026 292