የስታርትአፕ ዘርፍን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለማጎልበት ሲካሄድ የነበረው የ«Cursor AI Hackathon 2026» ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ።
==================
በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ለማጎልበትና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ቴክኖሎጂ ለማበልጸግ ያለመው «Cursor AI Hackathon Ethiopia 2026» ውድድር ከሐምሌ 18 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲካሄድ ቆይቶ በስኬት ተጠናቀቀ።
በውድድሩ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ እንደገለጹት፣ መሰል የቴክኖሎጂ ውድድሮች የወጣቶችን የፈጠራ እውቀቶችን ወደ ተግባራዊ የፈጠራ መር ቢዝነሶች በመቀየር የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እንደሚያፋጥኑ ገልጸዋል።
አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለዲጂታል ስታርትአፖች የሚያደርገውን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሀገር በቀል ችግሮችን የሚፈቱ መፍትሔዎችን ማመንጨት የነገዋ ኢትዮጵያን እድገት የሚያረጋግጥ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።
በውድድሩ ላይ የላቀ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማቅረብ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊ ቡድኖች የተለያዩ ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ የሃካቶን ውድድር ወጣት የፈጠራ ባለቤቶች በጋራ በመሆን ሀሳቦቻቸውን በተግባር የሚፈትሹበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ትልቅ መድረክ ሆኖ ማገልገሉ ተመልክቷል።
በመጨረሻም ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አዘጋጆችና አጋር አካላት ምስጋና የቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይም መሰል የፈጠራ መድረኮችን በስፋት በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ የስታርትአፕ ዘርፍ እድገት በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።
Forwarded fromMinistry of innovation and technology (MinT)
1July 27, 2026 106 1








