CHEFFE PRIMARY SCHOOL 2013: post #5330 — TG.ME

Forwarded fromLILiul Abat
ቀን- 07/12/2018ዓ.ም
ድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
 
ለጨፌ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በሙሉ
 
ጉዳዩ፡- የተማሪ ምዝገባን በተመለከተ የግንዛቤ ማስተካከያ ስለመስጠት
 
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የጨፌ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የትም/ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ ተማሪ ምዝገባ በነፃ ሆኖ እያለ የመመዝገቢያ ክፍያ ክፈሉ ተብለናል በሚል የተሳሳተ መረጃ እየተናፈሰ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ት/ቤቱ በቀን 17/11/2018ዓ.ም በወጣው ማስታወቂያ ላይ የተማሪ ምዝገባ ከክፍያ ነፃ እንደሆነ የተገለፀ ቢሆንም አሁንም ድረስ አንዳንድ ወላጆች ላይ ያልተስተካከለ መሆኑን ያጣራን ስለሆነ ማንኛውም ወላጅ የመመዝገቢያም ይሁን የልማት ክፍያ በተማሪ ምዝገባ ወቅት እንዳይፈፅም በድጋሚ እያሳወቅን ክፍያ ያልከፈላችሁ አንመዘግብም የሚል አካል ካለ ጥቆማ እንድታደርሱን ትብብራችሁን እየጠየቅን ማንኛውም እድሜው ለትምህርት የደረሰ ህፃን በሙሉ ወደ ት/ቤታችን በመምጣት በነፃ መመዝገብ የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡  
 
 
ት/ቤቱ!
❤6
August 13, 2026 1.2K 3 1