የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምረው ማየት ይችላሉ - የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸውን ማስፈንጠሪያዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ
https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ማቅረብና ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et፣ ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡
https://result.eaes.et/sms መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡








