#የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን - ሲዳማ ቡና ! #የ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍፃሜውን አገኘ ! ሲዳማ ቡና ሻምፒዮን የሆነበት የ 2018 የ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል። በሀዋሳ ከተማ በተደረገው የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 1ለ0 አሸንፏል። ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና 6️⃣8️⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ አመቱን አጠናቋል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ 5️⃣4️⃣ ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል። #ኮከብ ግብ አግቢዎች እነማን ናቸው ? - ታምራት እያሱ ( ፋሲል ከነማ ) - ናትናኤል ዳንኤል ( ንግድ ባንክ ) በ 1️⃣5️⃣ ጎል ኮከብ ግብ አግቢ ሆነው አጠናቀዋል። #እነማን ወረዱ ? - #ሽረ ምድረ ገነት - #ድሬዳዋ ከተማ - #መቐለ 70 እንደርታ እና - #አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረዱ ክለቦች ሆነዋል። #እነማን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አደጉ ? - #ጋሞ ጨንቻ እና - #ሀላባ ከተማ ወደ 2019 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አድገዋል። #የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በ 1️⃣8️⃣ ክለቦች መካከል የሚደረግ ይሆናል።
July 5, 2026 81