መጋቢት 28/07/18 ክፍል (2) * * *ለሪቫይቫል (ተሀድሶ )*** በፓስተር ጆን ምን አድርጌአለሁ ብሎ… — 🎤ቦርፎሪኮን🎸 — TG.ME

መጋቢት 28/07/18 ክፍል (2)
        * * *ለሪቫይቫል (ተሀድሶ )***
                                 በፓስተር ጆን
ምን አድርጌአለሁ ብሎ ራሱን የሚጠይቅ
የለም የነቢዩ የኤርምያስ ጩኸት !
                 8:6-12
<< አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ ማናቸውም፦ ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።
⁷ ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
⁸ እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል።
⁹ ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?
¹⁰ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
¹¹ የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ስላም ሰላም ይላሉ።
¹² አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ይሁዳ ከመማረኳ በፈት የተነገረ የነቢዩ ትንቢት ነው ።

በጉልህ አሁን ያለንበት ዘመናችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
          የነቢያት አገልግሎት
          የሀሰተኛ አስተማሪዎች
           የእረኛ ሳይሆን የሙያተኛ ፓስተሮች
           የሳይሆኑ ሐዋርያት ነኝ ባዮች ወዘተ...  
በምድራችን የእግዚአብሔር እንዳይሰራ እና በውጭ ላሉት ማሰብን ትተን በውስጥ ላሉት በጎች መስጋትና መጨነቀ የእለት ተለት ስራ ሆነዋል ።

       አሁን ነው አትመጣም ወይ ማለትን
ማዘውተር............ይቀጥላል ።
          
t.me/yekal_sink     share 🙏
Telegram
Pastor John official🇪🇹🇪🇷🇺🇸
በዚህ ቻናል በየእለቱ የቃል ስንቅ አዳድስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮች እናም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። 😒አይኔን አንስቼ ከሰው ላይ፣😔 ሀዘኔን ረሳው ኢየሱስን 😳ሳይ😁 ለአስተያየታችሁ http://t.me/hiyaw_kal
April 6, 2026 309