አስቂኝ ቀልዶች እናምርጥ ተረትና ታሪኮች: post #112 — TG.ME

🚕ታክሲ ውስጥ😂
ታክሲዉስጥ ከሗላ ተቀምጬ ከፊቴ ያለው  ወንበር ላይ የተቀመጠው ልጅ አጠገቡ ያለችውን ልጅ ገና ከመግባቱ ይጀነጅናት ጀመር...
  ልጁ፡ ሀይ ቆንጆ
ልጅቷ፡ ሀይ! (ኮስተር ብላ😠)
  ልጁ፡ ጠፋሽ ምነው?
ልጅቷ፡ መብራት ሀይል ገብቼ ነው::
  ልጁ፡ ወዴት ነሽ?
ልጅቷ፡ ወደፊት፡፡
  ልጁ፡ ልሸኝሽ? (እንዴ ታክሲውስጥ     መሆኑን ረሳው መሰለኝ)
ልጅቷ፡ይቅርብህ  ትጠፋለ የ፡፡
  ልጁ፡ ሰፈርሽ የት ነው?
ልጅቷ፡ ለልማት ፈርሷል፡፡
  ልጁ፡ አረ ተጫዋች ነሽ፡፡
ልጅቷ፡ አይ አሰልጣኝ ነኝ¡
  ልጁ፡ ስልክ አለሽ?
ልጅቷ፡ network የለውም፡፡
  ልጁ፡ ተመቸሽኝ!
ልጅቷ፡ ከታክሲው ነው፡፡
  ልጁ፡ ማታ ለወክ ትወጫለሽ?
ልጅቷ፡ መብራት ስለማይኖሮ ይጨልማል፡፡
ልጁ፡ አንድ ነገር ላስቸግርሽ?
ልጅቷ፡……………





  😜እኔ ፦ ወራጅ! ወራጅ! ወራጅ አለ፡፡ እነሱን እየሰማው ቤቴን አለፍኩት ፡፡ከዚ በኃላ የተባባሉትን አልሰማውም፡፡ወርጄ ወደቤቴ🏃ቅደደው 😂
😂😂

Join us//👉 @bfunn
January 18, 2023 10K 68