አስቂኝ ቀልዶች እናምርጥ ተረትና ታሪኮች: post #115 — TG.ME

የማዳመጥ ኃይል

◽️ብዙ ስታዳምጥ ብዙ ስለማታወራ ስህተት አትሰራም።

◽️ብዙ ስታዳምጥ ሳታስበው ብዙ እያወክ ነው።

◽️ሰዎችን በተመስጦ ስታደምጣቸው እንደምታከብራቸው ስለሚያስቡ ካንተ ጋር እንደመሆን የሚያስደስታቸው ነገር የለም። (በተለይ ሴቶች ለሚያደምጣቸው ወንድ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ)

◽️ሁሉንም አድምጠህ በመጨረሻ የምትናገር ከሆነ ያንተ ሀሳብ የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው።

ወዳጄ ምንም ቢሆን አይጎዳህም አሪፍ አዳማጭ ሁን!

መልካም ቀን🫶
Join us//👉 @bfunn
January 18, 2023 12.3K 32