አስቂኝ ቀልዶች እናምርጥ ተረትና ታሪኮች: post #100 — TG.ME

ለፈገግታ😁😅😂

ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር #ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ ወይኔ #ባሌ!😊" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።💁‍♀😄

#ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።💪

ከዚያም በድል #አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ። 😎
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን #ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"😃
" #እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"😳
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።
😅😂😂

የሰው ልጅ #ጎዶሎ ነው የተሟላ አይደለም፣ ፍፁምነት #ለፈጣሪ ብቻ ነው‼️
ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት ... በሀሳብም በአካልም እንዲሞላሉ ተደርገው ነው እግዜሩ የፈጠራቸው። አንዱ የጎደለው ሌላው አለው። አንዱ የማይችለዉን ሌላው ይችለዋል ፣ ለአንዱ የማይታየው #ለሌላው ይታየዋል።

ለመናናቅ፣ ለመገፋፋትና ለመለካካት ሳይሆን ሕይወትን #አብረን እንድንኖር፣ ፈተናዎቿንም አብረን እያሸነፍን ወደ ገነት እንድንጓዝ ነው ፈጣሪ ወደዚህች ምድር ያመጣን።

አንዱ የሌላኛዉን ሀሳብ ጆሮ ሰጥቶ ያድምጥ‼️

አይናናቅ፣ አያጣጥል።🤗

Join us//👉 @bfunn
December 31, 2022 6.9K 69