የዐማራ ፋኖ ትግልና የዐማራ ወጣት በጸረ ዐማራ ኃይሎች አፈሳ ነገር ‼️ ለሁሉም የዐማራ ፋኖ ኃይሎች‼️ እንደ… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME

የዐማራ ፋኖ ትግልና የዐማራ ወጣት በጸረ ዐማራ ኃይሎች አፈሳ ነገር ‼️ ለሁሉም የዐማራ ፋኖ ኃይሎች‼️ እንደ ብሔርተኝነት እንቅስቃሴ በዚህ ወቅት ይሄን ዜና መስማት ለዐማራ የብሔርተኝነት ትግል ትልቅ የልብ ስብራት ነው። ይሄን አጋጣሚ መደበኛ ውጊያ እያደረገ ያለው ጠላት፣ ተራ የሚጠብቀው ጸረ ዐማራ ኢትዮጵያኒስት ኃይል እየተጠቀሙበት ነው። የውጩና የቀጠናው ፖለቲካዊ ሀገራትም ቢሆን የዐማራ ትግል በረግረግ ጭቃ የተያዘ ወይንም ሰማጭ መርከብ አድርገው መሳላቸው ማሳያ ይሆናል። የዐማራ ፋኖ በየትኛውም ጠርዝ ያለው ፖለቲካዊ አይኑን እያጎላ የዐማራን ህልውናዊ ጥቅም እየዘነጋው ይመስላል። የዐማራ ወጣቶች አፈሳ የዐማራ የህልውና ጉዳይ ነው። ይሄ ወጣት በየትኛውም የጦር ግንባር ሰለባ የሚሆን ፤ በሁለተኛም የራሱን የዐማራ ህዝብ የሚጨፈጭፍ የምሳር መግጠሚያ እጀታ በመሆን ሊያገለግል የተመረጠ ነው። ይሄ ሁለቴ ሞት ነው። የዐማራ ፋኖ አብዛኛው ቀጠናዎችን ከገጠር እስከ ከተማ ተቆጣጥሯቸዋል። ፋኖ ይሄን ባደረገበት ቀጠና የጠላት ኃይል የዐማራ ወጣቶችን አፍሶ የራሱ ወታደር ሊያደርጋቸው አይገባም። የወጣቶችና የማህበረሰቡ የራሱ የሆነ ድክመት ነው ብንል እንኳን ፤ እኛ የህልውና ታጋዮች ይሄን የራሱ ጉዳይ ብለን የምንተወው አይሆንም። በቅድሚያ ፋኖ ያልነቃውን ሰፊ ማህበረሰብ ማንቃት፣ በጥርጣሬና በአሉባልታ እንዲሁም መጥፎ ምሳሌ በሆኑ የፋኖ መሪዎች የራቀውን አቅርቦ፣ ልቡን አማሎ የዐማራ ወታደሮች እንዲሆኑ ሰፊና ወጥ የሆነ ፕሮግራምና ስልት አውጥቶ ሊሰራበት ይገባል። ሁለተኛው ደግሞ ተቋርጦ ቀርቶ፣ ፋኖም በአስቸኮይ ስራውን ሳይሰራ ቀርቶ በዐማራ ወጣት ላይ የሚደረግን አፈሳ፣ በዐማራ ህልውና ላይ የተቃጣ ሰይፍ አድርጎ በመቁጥር በወታደራዊ ኦፕሬሽ የማስመለስ ስራ መስራት ይኖርበታል ! በዚህ በእኛው የፖለቲካና የብሔርተኝነት ድክመት ህዝባችን ዋጋ ሲከፍል፣ ተገዶ የገባን የዐማራ ቀጣት የጠላት ወታደርም ስበን ስናስከዳና ስናጠቃ አንኖርም !! ፋኖ አላሰለጥነው ሲል ጠላት በሰፊው በር ገብቶ እየተጠቀበት ነው። ይሄን ለማድረግ የተቀናጀ ስራ መስራት ይኖርብናል። ፋኖ ወጣቶችን ስልጠና ሰርቶ የዐማራ ዘብ ለማድረግ የቅድሚያ ፍላጎት፣ ተነሳሽነትና ዓላማ የሚጠይቅ ሁኖ ፤ ይሄን ለማድረግ ሰፊ የሆነ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ ነውና በዛ እንተጋገዛለን !

November 28, 2024 777