እስማኤል ቃኒ እንደ ኢሊያሁ ኮህን ‼️
ህልውና እንደዚህ ነው !
ሁሌም የእስራኤልና ከማህጸናቸው የወጣው የሞሳድ ነገር እንዳስገረመኝ ነው። ይሄ እኔን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻቸውንም ከመጥላታቸው ባሻገር ማስገረሙ እንዳለ ነው።
ከዚህ የምንማረው ስለህልውና ትግል ቁልፍ ሚስጢር ነው። የህልውና ትግል እንደዚህ ነው። የህልውና ትግል ምን ይመስላል ካላችሁ የእስራኤል ጽዮናዊ ትግልን ይመስላል ነው መልሱ። ስለህልውና ትግል በልኩ የሚታገሉ እንስሳትና እስራኤላውያን ናቸው። የእኛው ማስመሰልና የፖለቲካ ንግድ ነው !
ንቦችን ተመልከቱ፡ ማራቸውን ብትነኩ ወይንም ወደ ቀፎው ተጠግታችሁ ጥላችሁ ቢከብዳቸው ወይንም ጠረናችሁ ቢሸታችሁ ተጠራርተው ያለርህራሄ ነድፈው ያባርሯችኋል። ሌሎችም እንስሳት ከንብ ከፍተው ይከላከላሉ ያጠቃሉ፤ ልዩ ስፍራ ይይዛሉ !
በአልችልም ባይነት የሚጠቁት እጽዋት ናቸው። እጽዋት እንቅስቃሴ ያቸው ውጫዊ ባለመሆኑ ተንቀሳቅሰው ማምለጥ ወይንም መዋጋት አይችሉም። ምርጫቸው ጡንቻቸውን አጠንክረው ማልቀስ (irritate) ማድረግ ብቻ ነው። የዐማራ ብሔርተኝነትም እንደ እጽዋት ያለ ትግል ነው። ፖለቲካዊ ተራምዶ የለውም !
ለማንኛውም ወደ ጉዳዬ ልግባ። ሰውየው እስማኤል ቃኒ ይባላል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ ከፍተኛ ብርጋዲየር ጀነራል ነው። በ 20 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ቡድንን ተቀላቅሎ በተለያዩ ምድቦች አገልግሏል። 1980-1988 በተደረገው የኢራን-ኢራቅ ጦርነት የኢራንን ጦር እየመራ በጀብድ ተዋግቷል።
ጥር 3, 2020 በኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ አማካኝነት በአሜሪካ ጥቃት የተገደለውን የቀድሞውን የኢራን የጦር አዣዥ ሱሌይማንን ለመተካት አዲስ አዛዥ ሁኖ ተሹሟል። በካሜኒ አማካኝነት ይህ ሰው ከጠባቂዎች ውስጥ “በጣም ያጌጡና ክብር ካላቸው አዛዦች” መካከል አንዱ በመባል በልዩ ዝናና ክብር የሚገባው እንደሆነ ተወድሶ በ 1997 የIRGC ዋና አዛዥ ሁነው ተሾሙ ።
በመጨረሻም እስራኤል-የአረቡ ዓለም ለአንድ አመት ገዳማ እያደረጉ ባሉት ጦርነት የእስራኤሉ ሞሳድ የኢራን፣ የሂዝቦላ፣ የሃማስ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ አዛዦች እስከ ቤት ጓዳቸው ገብቶ እየገደላቸው ነው። ይሄ ግድያ ያስደነገጣቸው የኢራን ባለስልጣናት በኤሊያሁ ኮህን ጊዜ እንደሆነው እርስ በእርስ ሲጠራጠሩ እስማኤል ቃኒ የእስራኤል የስለላ መረብ የሞሳድ ኤጀንት ሁኖ አገኙት። በከባድ ምርመራ ውስጥ እያለ እስማኤል በልብ ድካም ራሱን ስቷል። ራስ አሳሳቱ በራሱ ሞሳድ በቅርብ ርቀት በሪሞት ኮንትሮል እያደረገው ነው ብለዋል።
ለማንኛውም ገድሉ ኤሊያሁ ኮህንን ካስናቀ ፕሮፋይል እንቀይራለን። ከሞሳድ ሙሉ መረጃውን በፍለጋ ላይ ነን።
የህልውና ትግል እንደዚህ ነው !!
1October 20, 2024 658 1