መነሻችን መድረሻችንም ነወ፦ መርህ ማለት ሊታለፍ፣ ሊታጠፋ፣ ሊሻርና ሊነካ የማይገባው አደገኛ መስመር ማለት ነው። ይሄ ነው መርሃችን። የዐማራ ትግል ከመነሻችን አንዱ ርስት ሲሆን መዳረሻችን የዐማራን ታሪካዊ ርስት እንደገና መመለስ ነው። ይሄ መዳረሻችን ነው። በኢትዮጵያ አዳራሽ ደማቅ ቀለም ተቀብቶ የዘር ማጥፋት ድርጊት የተፈጸመበት፣ ምልክት የተሰጠው ዐማራ መፍትሔ ብሎ የሚያስባቸው ከብአዴን ልብና አእምሮ ጀምሮ እስከ እያንድአንዱ ዐማራ ይለያያሉ። በዚህ የዘር ማጥፋት ድርጊት ውስጥ ያለው ዐማራ "የህልውና ጥያቄ" አለብኝ ብሎ ሲጠይቅ አይኖርም። አሁን መልስ ሊሰጥ እየታገለ ነው። አንድአንዱ የዐማራን ትግል የዐማራ የህልውና ጥያቄ ጀሮ እንዲያገኝ ማድረጊያ አድርጎ የሚቆጥረው አለ። ህልውናው የሚከበርበት መፍትሄ እየፈለገ ነው። እሱንም ራሴው እመልሰዋለሁ ብሎ ገብቷል። ከእነዚህ መፍትሄዎች ውስጥ አንዱ ዐማራ ለመጭው ረጅም ዘመን ህልውናው ተከብሮ እንዲኖር "ሀገረ መንግስት መገንባት" አለበት የሚል ነው። ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ አንድ ጹሁፍ ሲዘዋወር ተመለከትኩ። ይሄም ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ እንደ ይሁዲው ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን ይሆናል ብለን ከምናስባቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ ነወ። ይሁን እንጅ ሰሞኑን "መነሻችን ዐማራ መድረሻችን ዐማራ የሚባል ርባና ቢስና የማይጨበጥ ነገር" የእንደማያስቡ ተናግሯል። ጠበቃ አስረስ ለፖለቲካ ንግግር (political correctness) የሚባል ነገር ስላለ ይሆናል ይሄን የተናገረው። "መነሻችን ዐማራ መድረሻችን ዐማራ" በሚለው ንግግር ላያምንበትም ይችላል። እሱ ግለሰባዊ መቅቱና እምነት ወይንም አስተሳሰቡ ነው። ነገር ግን ስህተቱ "መድረሻችን ዐማራ" የሚለው ንግግርም ሆነ ዓላማ ርባና ቢስና የማይጨበጥ እንደሆነ ደፍሮ መናር ነበረበት ብዬ አላምንም። ምክንያቱም ለዚህ ዓላማ ከጎኑ ሁነው የወደቁ፣ እየተዋደቁ ያሉ ኃይሎች አሉ። በሚሊዬን የሚቆጠር ወጣት ይሄን ሀሳብ እንደሚናፍቀው ከመናፈቅም ባሻገር ዋጋ እየተከፈለበት እንዳለ፣ በአዳኝነትም የሚከተሉት እንዳሉ ግምት ውስጥ ማስገባት ነበረበት። ክፍፍል በበዛበት ፋኖ ሌላ ክፍፍል አንፈጥርም በሚል ጭምት ሀሳብ እንጅ አንድ ክፍለ ጦር ለዚህ ሀሳብ እስከ ፍጻሜና ቀራኒዮ ድረስ የሚዘልቅ የፋኖ ኃይል ማዋለድና ማቆም የሚቻልበት ሁኔታ ነበረ። መሬት ላይ ይሄ ኃይል ያለና ለዚህም የፋኖን አንድነት የሚጠብቅ፣ አሁን ላይ ይሄን ማንሳት ከአለው ክፍፍል ጋር ተደምሮ ሌላ መጓተት እንደሚያመጣ ታስቦበት የተራዘመ እውነት ነው። ይሄ ባይሆን እንኳን ይሄን ትልቅና የዐማራ የህልውና ጥያቄ አካል፣ ጥያቄም ብቻ ሳይሆን መልስ ሰጪ ሀሳብ በዚህ ደረጃ ለፖለቲካል ኮሬክትነስ ሲባል "ርባና ቢስና የማይጨበጥ" በማለት ሊገለጽ የማይገባው ነበር። ነገ ሌላ ቀን ነው እያደርርን እናያለን !
መነሻችን መድረሻችንም ነወ፦ መርህ ማለት ሊታለፍ፣ ሊታጠፋ፣ ሊሻርና ሊነካ የማይገባው አደገኛ መስመር ማለት… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME
October 19, 2024 488