ትምህርት 10- የታላቁ ተጋድሎ ፍጻሜ እና ሰማያዊቷ አገር ======================== ውድ ተማሪዎች: ወደ 10ኛው ትምህርታችን ደርሰናል:: እስካሁን የረዳንን ጌታ እናመሰግነዋለን:: መልካም የሰንበት እረፍት እንዳሳለፋችሁ እምነታችን ነው:: 10ኛው ትምህርት በክፉ እና በመልካም: በሰይጣን እና በክርስቶስ: በሐሰት እና በእውነት መካከል ለብዙ ሺህ አመታት የተደረገውን የታላቁን ተጋድሎ ድምዳሜ ይዳስሳል:: ምንም እንኳን ክፋት ቢበዛም: ሞት እና ስቃይ ምድሪቱን ቢያጥለቀልቃትም የሕይወትና የሰላም አምላክ ክፋትን አስወግዶ በዩኒቨርስ ላይ ጽድቅን የሚያንሰራፋበት ጊዜ ሩቅ አይደለም:: ኃጢአት እና የኃጢአት ደራሲ የሆነው ሰይጣን ሲወገድ በኢየሱስ ደም ልብሳቸውን ያላጠቡ እና ከኃጢአት ጋር ያልተላቀቁ የዘላለም ሞት ይጠብቃቸዋል:: የሁለተኛው ሞት ተካፋይ እንዳንሆን እውነትን አውቀን ጥሪውን ተቀብለን የሰማይ መንገደኛ የሆነውን እግዚአብሔርን ሕዝብ እንቀላቀል:: መልካም ጥናት
July 20, 2026 8.7K 3 6