ማቴዎስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።
²⁴ እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።
²⁵ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት።
²⁶ እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
²⁷ ሰዎቹም፦ ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ።
"ሥራህን አስቤ ሳይሆን መኖርህን አስቤ ልመንህ!
የተገለጠውን የእግዚአብሔር ስራ እያዩ እምነትን ማጣት፤ የእግዜርን መኖር በጭፍንነት መካድ ያለንበት የአሁን ዘመን ትውፊት ከሆነ መሰንበቱን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ነገር ነው።
እግዚአብሔር ሲሰራ እያየን ማመን በከበደበት ዘመን ቆመን ይበልጡን በሰው ሚዛን "እግዜር የለም .... ፀጥ አለ!" በሚባልበት ሰዓት በዝምታው ውስጥ መኖሩን በማሰብ ወዳለው እምነት ማደግ ምንኛ መታደል መሰላችሁ..... ከማዕበሉ ጩኸት ጋር መስማማት በሚቀልበት በዛ ሰዓት ከእግዚአብሔር ዝምታው ስር በእምነት መቆየት፤በሰውኛ ልክ ከሚመስሉ ጩኸቶች፣ ማያስተርፉ ከሚመስሉ ነፋሳት ይልቅ፣ ልክ ከማይመስለው ግና የልክነትን ሚዛን ከሚሰብረው፣ የነገ ምስጋና ከሚሆነው ዝምታህ ጋር መተባበር ወዳለው እምነት ማደግ፤ ዝምታው ውስጥ ካለው መሰራት በኋላ ያለውን የጌርጌሴኖን ስራ ገብቶት መፅናት ሚችልበትን እምነት የለበሰ ሰው ምንኛ ታደለ.......
ጌታ ሆይ...ለአብሮነትህ ዋስትና ስራህ አይሁነን!.... የእጂህ ላይ ሳይሆን የፋትህ ብርሃን ላይ ቀልባችን እንዲያርፍ... በአብሮነትህ ውስጥ ስራህን እንይ። ስራህ አብሮነትህን ሳይሆን አብሮነትህ ስራህን ይጠቁመን። .....አልያማ ያልሰራህ የመሰለኝ ቀን፣ ዝም ያልከኝ ቀን፣ ማዕበሉ ያገላበጠኝ ቀን እንገዳገዳለው። እምነቴን ስራህ ላይ ሳይሆን አብሮነትህ ጋር አርገው። ማዕበሉን ፀጥ ታስብላለህ ብዬ ሳይሆን በማዕበሉ ውስጥ አብረኸኝ ነህ ብዬ ልመንህ ........
ያኔ አልንገዳገድም .... ከጩኸቱ ጋር አብሬ አልጮህም፤ ለጩኸቱ ጩኸት አላዋጣም። ዝምታህ እኔን መያዝህን አይጋርድብኝ፤ .....ስጠፋ አይገድህምን አልለውም፤ ስደቢው ከሚሉት ጋር አልተባበርም፤ብድንም ባልድንም ማለት አይከብደኝም! አብሮነትህ ሲቀድምልኝ፤ መታመኛዬ አብሮነትህ ጋር ሲሆን አይኔን ካንተ አልነቅልም ! ያኔ... ለምን ማለቴ ይለየኛል ።
እምነቴ ዝምታህ በማይገታው አብሮነትህ ላይ እንጂ ዝም ያልክ ቀን በሚጋረድብኝ (እያለ በማላየው) ስራህ ላይ አይሁን......ዝም ስትል እንኳ የኛ አባት አንተ አዋቂ ነህ ለዝምታህ አትታረምም!!ለዝምታህ በአብሮነትህ ታምነን አሜን ካለማለት እኛን አርመን እንጂ!!
ከዝምታ በኋላ ያለውን ስራህን ሳይሆን በዝምታ ውስጥ ያለኸውን አንተን ልመንህ!!
🤲🤲🤲🤲🤲አሜን
@wcudisciple
