ትምህርት 9:- ክርስቶስ ሊቀ ካህናችን ======================== ውድ ተማሪዎች: የክርስቶስን… — የደቀ መዝሙርነት ት/ቤት - Classroom — TG.ME

ትምህርት 9:- ክርስቶስ ሊቀ ካህናችን ======================== ውድ ተማሪዎች: የክርስቶስን ምድራዊ ሕይወት: ሞት እና ትንሳኤን ከዚህ በፊት በስፋት ተምረናል። ባለፊት ሳምንታት በተማራችሁአቸው ትምህርቶች እንደተባረካችሁ ሙሉ እምነታችን ነው። አሳልፎ በመስጠት የኃጢአት ዋጋ የሆነውን ሞት በእኛ ፋንታ በመቅመሱ የእሱን ሕይወት ያጋራን ጌታችን የተመሰገነ ይሁን! በጸጋ የዳን ሰው በቅድስና ሕይወት እንዴት መኖር እንዳለበት፡ የእግዚአብሔርን ሕግጋት እንዲሁም አብዛኛው ሕዝብ ሳያውቅ የሚተላለፈውን የሰንበትን እረፍት አጥንተናል። በተጨማሪም ሰው ሲሞት ምን እንደሚሆን፤ ሙታን አሁን ያሉበትን ሁኔታ፤ ነፍስ አትሞትም የሚለው አስተምህሮ ትልቅ ስህተት እንደሆነ እና ከሰይጣን ማታለያ መጠንቀቅ እንዳለብን ባለፉት 2 ሳምንታት ተምረናል። በዚህ ሳምንት ደግሞ በሰማይ አዳኛችን የሚያደርገውን አገልግሎት እናጠናለን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ደሙ በሰማይ ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ ስለ እኛ ሊማልድ በአብ ፋት ቆሟል:: የምድራዊው ቤተ መቅደስ የሰምያዊው ጥላ በመሆኑ ተወግዷል:: የሰማዩ ቤተ መቅደስ ግን አሁንም ለሰዎች ደህንነት የሚሆነው የክርስቶስ ደም ኃጢአትን እየፋቀ ጸጋ እና ምሕረትን ለአማኞት እያዳረሰ ነው! በዚህ ሳምንት - በሰማይ ቤተ መቅደስ የሚደረገውን አገልግሎት እና የክርስቶስን ዳግም ምፃት እንዳስሳለን! መልካም ጥናት!

👍16❤12
July 6, 2026 11.3K 7