የቤተክርስቲያን በዓላት" መግቢያ በዓል:- ማለት የተቀደሰ የተከበረ ልዩ ክቡር ቀን ማለት ነው ። በዓላት… — አርያም ስቱዲዮ _ Areyam Studio — TG.ME

Forwarded fromRARadar Cripto Pro
"የቤተክርስቲያን በዓላት"  መግቢያ

በዓል:- ማለት የተቀደሰ የተከበረ ልዩ ክቡር ቀን ማለት ነው ። በዓላት በልምድ የሚከበሩ ወይንም
ስራን ላለመስራት ተብሎ የተፈጠሩ አይደሉም።
የመንፈሳዊ በዓላት  መገኛ ምንጫቸው ሃይማኖት ነው ። በብሉይ ኪዳን የሚከበሩ ብዙ ዓይነት በዓላት ነበሩ ። የበዓላት ሁሉ መሰረት ግን ቀዳሚት ሰንበት ናት ። ሰንበት ማለት እረፍት ማለት ነው ። 

ዘፍጥረት 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።
³ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።

👉 በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ቅዳሜ እና እሁድ ነው ቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ትባላለች እሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስትያን ትባላለች ።

👉 ሰንበተ ክርስትያን እሁድ ጌታ ፍጥረታትን መፍጠር የጀመረበት ፣ የተጸነሰበት ፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሳበት ናትና ይች ዕለት ትከበራለች ።

ስለ በዓላት የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች👇

ዘጸ 16:23 ፣ዘጸ 20:8 ፣መዝ 41:4 ፣መዝ 75 :10 ፣ ዮሐ 10:22 ፣ ሐዋ 20:7

👉በቤተክርስቲያን "ዓበይት በዓላት" የሚባሉት የጌታ በዓላት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻቸው 👇

1. ብስራት...ሉቃ 1:26
2.ልደት... ሉቃ 2:7
3.ጥምቀት....ማቴ 3:13፣ሉቃ 3፣21
4.ደብረ ታቦር....ማቴ 17:1 ፣ማር 9:21 ፣ሉቃ 9:28
5.ሆሳዕና....ማቴ 21:1
6.ስቅለት....ሉቃ 23:33
7.ትንሳኤ....ሉቃ 24:5
8.ዕርገት....ሉቃ 24:50
9.ጰራቅሊጦስ....ሐዋ 2:4

👉 በቤተክርስቲያን "ንዑሳን በዓላት" የሚባሉት

1.መስቀል...ማቴ 27:1 ፣1 ቆሮ 1:18
2.ስብከት.....ዮሐ 1:44 ፣ ዕብ 11:1
3.ብርሃን.....መዝ 42:3 ፣ኢሳ 9:2 ፣ዮሐ 8:12
4.ኖላዊ....መዝ 22:1 ፣ዮሐ 10:1-22 ፣ 1ጴጥ 2:25
5.ግዝረት.....ዘሌ 12:3 ፣ሉቃ 2:21
6.ልደተ ስምዖን....ሉቃ 2:25
7. ቃና ዘገሊላ....ዮሐ 2:1
8.ደብረ ዘይት.... ማቴ 24
9. መስቀል (የመጋቢት ወር) 

የቤተክርስቲያን ዓበይት እና ንኡሳን በዓላት የሚባሉት በቀጥታ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደሚገናኙ ልብ ማለት ያስፈልጋል ።

እግዚአብሔር ይችን ቤተክርስቲያን ስለሰጠን የተመሰገነ ይሁን 🙏
❤3
March 13, 2026 255 1