ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ በሰማይ ባረገ ጊዜ አምላክ አዶናይ ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ መንበሩ ፊት ቆመው የሚያመሰግኑት… — አርያም ስቱዲዮ _ Areyam Studio — TG.ME

ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ በሰማይ
ባረገ ጊዜ አምላክ አዶናይ


ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
መንበሩ ፊት ቆመው የሚያመሰግኑት
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
በፍፁም ፍርሃት ዘወትር ሚሰግዱለት
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ሥግው ቃል ክርስቶስ ሲያርግ አዩትና
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
መላእክት ተቀኙ በአዲስ ምስጋና

/አዝ =====

ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
እርሱን ለማሳረግ መላእክት አልመጡም
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ከፍ ከፍ ሊያደርጉት ሠረገላት የሉም
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ደቀመዛሙርቱን በተስፋ አፅንቶ
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
በስልጣኑ አረገ ደመናን ተጫምቶ

/አዝ =====

ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ዲያቆን
ዐቢይ ዜማ ተሠመዓ
ጠላቱን በመውደድ የመሰለ አምላኩን
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
በድንጋይ ሲወገር መታገስ የቻለው
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ጌታን በአባቱ ቀኝ ሆኖ ስላየ ነው

/አዝ =====

ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
እንዲህ እንዳየነው በክብር ሲወጣ
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
እናምናለን እኛ ዳግመኛ እንዲመጣ
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ወደ እርሱ ይመለስ ይዘጋጅ ልባችን
ዐቢይ ዜማ ተሠማዓ
ማደሪያው ንፁሕ ልብ ለሆነ ጌታችን


├───────────────
├የሕብረት ዝማሬ
├───────────────

•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•
ዓቢይ ዜማ ተሰምዓ
June 4, 2025 508