የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?
(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)
- የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል።
- ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት።
- ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን 550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው።
- ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው።
- ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል።
#በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል)
1. አዲስ አበባ 32.3%
2. ሀረሪ 22.67%
3. አፋር 15.6%
4. አማራ 15.56%
5. ድሬዳዋ 11.29%
6. ትግራይ 11.2%
7. ኦሮሚያ 10.53%
8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23%
9. ሶማሌ 9.2%
10. ሲዳማ 6.95%
11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12%
12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82%
13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92%
14. ጋምቤላ 3.74%
በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል)
1. ኦሮሚያ ➡ 20,807 ተማሪዎች
2. አዲስ አበባ ➡ 18,646 ተማሪዎች
3. አማራ ➡ 15,225 ተማሪዎች
4. ትግራይ ➡ 3,146 ተማሪዎች
5. ደቡብ ኢትዮጵያ ➡ 3,011 ተማሪዎች
6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ➡ 2,800 ተማሪዎች
7. ሲዳማ ➡ 1,827 ተማሪዎች
8. ሶማሌ ➡ 1,616 ተማሪዎች
9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ➡ 835 ተማሪዎች
10. አፋር ➡ 705 ተማሪዎች
11. ሀረሪ ➡ 599 ተማሪዎች
12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ➡ 457 ተማሪዎች
13. ድሬዳዋ ➡ 410 ተማሪዎች
14. ጋምቤላ ➡ 280 ተማሪዎች
- ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው።
- ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል።
ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ?
• ኦሮሚያ 156
• አማራ 98
• ደቡብ ኢትዮጵያ 86
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69
• ትግራይ 48
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22
• አፋር 21
• ሲዳማ 16
• ሶማሌ 9
• ድሬዳዋ 5
• ሀረሪ 3
• ጋምቤላ 2
• አዲስ አበባ 1
- ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል።
በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ?
• ኦሮሚያ 37
• አዲስ አበባ 24
• አማራ 8
• ደቡብ ኢትዮጵያ 4
• ትግራይ 4
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3
• ሲዳማ 2
• አፋር 1
• ድሬዳዋ 1
• ሀረሪ 1
• ሶማሌ 1
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1
- በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም።
- የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ?
• በተፈጥሮ ሳይንስ •
🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ
🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ
• በማህበራዊ ሳንይንስ •
🥇 ከወንድ 👉 576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት
- ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል።
- ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ።
- ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን።
- ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ።
- ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል።
📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia














