የመንገድ ጥገና ሥራ ማጠናቀቂያ መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከአያት 49 ወደ ፊጋ… — AACRA — TG.ME

የመንገድ ጥገና ሥራ ማጠናቀቂያ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከአያት 49 ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ ላይ 72 ድልድይ አካባቢ የመንገድ ጥገና ሥራ ለማካሄድ ከሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መንገዱ በከፊል ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት በክረምቱ ወቅት በአካባቢው ይከሰት የነበረውን የጎርፍ አደጋ ስጋት በጊዜያዊነት መቅረፍ የሚያስችል አሰቸኳይ የጥገና ሥራ በማጠናቀቅ፤ ከነገ ረቡዕ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ መንገዱ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት የሚደረግ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።
የመንገዱ ተጠቃሚዎች ለጥገና ሥራው መቀላጠፍ ላበረከቱት አውንታዊ አስተዋጽኦ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በዚህ አጋጣሚ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
በዚህ አካባቢ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ያለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የግንባታ ሥራ በቀጣዮቹ 3 ወራት ውስጥ የሚጀመር መሆኑን ከወዲሁ ሲገልፅ ከፍ ባለ አክብሮት ነው።
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
❤4👍1
August 26, 2026 1.9K