የሕይወት ማዳን ስጦታ አዲስ አበባ፣ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (አ.አ.ከ.መ.ባ)፡- "በሰብዓዊነት አንዲት… — AACRA — TG.ME

የሕይወት ማዳን ስጦታ
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (አ.አ.ከ.መ.ባ)፡- "በሰብዓዊነት አንዲት ጠብታ ደም እንለግስ፤ ህይወት እናድን" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሠራተኞች የደም ልገሣ እያካሄዱ ነው፡፡
በደም ልገሳው ላይ የተሳተፉ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች፤ ደም መለገስ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ መሆኑን ገልፀው፤ በተቋሙ ባህል እየሆነ የመጣውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማስቀጠል፣ በደም ልገሣ መርሃ-ግብር መሳተፋቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
በድንገተኛ አደጋዎች እና በሌሎች ምክንያቶች ሳቢያ ሊፈጠር የሚችለውን የደም እጥረት ችግር ለማቃለል፣ የደም ልገሣ አፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው የጠቆሙት የመርሃ-ግብሩ ተሣታፊዎች፤ እያንዳንዱ ዜጋ እንዲህ ባሉ ሰብዓዊ ተግባራት ላይ ሊሳተፉ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች፤ የተቋሙን ዋነኛ ተልዕኮ ለማሳካት ከሚያደርጉት ጥረት ጎን ለጎን፤ በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ አርዓያነት ያለው ሚናቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በዋናው መስሪያቤት ቅጥር ግቢ እየተካሄደ በሚገኘው የደም ልገሳ መርሃ-ግብረ ላይ፣ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ የተቋሙ ሠራተኞች እና የሥራ መሪዎች ተካፋይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡
❤6
August 31, 2026 940