Addis Intel: post #4655 — TG.ME

✴️ OpenAI ለ100,000 ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሉን በነጻ የሚሰጥበትን አዲስ ፕሮግራም ይፋ አደረገ

👉ኩባንያው ChatGPT for Academic Researchers የተባለ አዲስ አሰራር የዘረጋ ሲሆን፣ ይህም ሳይንቲስቶች፣ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኢንጂነሮች የከፍተኛ ደረጃ AI ሞዴሎችን በነጻ እንዲጠቀሙ ዕድል ይሰጣል።

👉 አሰራሩ በመጀመሪያ ለ10,000 ተመራማሪዎች ክፍት የሚደረግ ሲሆን፣ እስከ 2027 ደግሞ ቁጥሩን ወደ 100,000 ለማሳደግ ታቅዷል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሎችን፣ የዳታ ሴኪዩሪቲ ጥበቃን፣ እስከ 4 ከሚደርሱ የቡድን አባላት ጋር አብሮ የመስራት ዕድልን እና የተለያዩ የስልጠና ድጋፎችን ያገኛሉ።

👉 ይህ እርምጃ ተመራማሪዎች በጽሁፍ እና በሰነድ ስራዎች የሚያባክኑትን ጊዜ በመቀነስ ትኩረታቸውን አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶች እና ምርምሮች ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል።

🤩 @AddisIntel
❤1
July 30, 2026 27