Addis Intel: post #4660 — TG.ME

Google DeepMind የታዋቂውን AlphaFold ቡድን አባላት በተለያዩ የ AI እና የሳይንስ ፕሮጀክቶች ላይ በመመደብ ኦሪጂናል ቲሙን በትኗል

➡️ኩባንያው ትኩረቱን በ Gemini ወደሚመሩ የ AI ፕሮጀክቶች በማዞሩ የ AlphaFold ተመራማሪዎች ወደ Genomics፣ Enzyme design፣ Nuclear fusion እና Gemini ፕሮጀክቶች ተዛውረዋል። በተጨማሪም የተወሰኑት ተመራማሪዎች Alphabet ስር ወደሚገኘው Isomorphic Labs የተሸጋገሩ ሲሆን የኖቤል ተሸላሚው John Jumperን ጨምሮ አንዳንዶቹ ደግሞ ኩባንያውን ለቀው ወደ Anthropic ተቀላቅለዋል።

➡️ይህ የቡድን መበተን የ AlphaFold ፕሮጀክት ማብቂያ እንዳልሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ዳታቤዝ ከ200 ሚሊዮን በላይ የፕሮቲን ስትራክቸሮችን ይዟል። በተጨማሪም AlphaFold 3 እና በ AI የሚመራው የመድኃኒት ግኝት ምርምር በ DeepMind እና Isomorphic Labs ስር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

🤩 @AddisIntel
❤1
July 31, 2026 37