3:30Watch in Telegram OpenAI ለ100,000 ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሉን በነጻ የሚሰጥበትን አዲስ ፕሮግራም ይፋ አደረገኩባንያው ChatGPT for Academic Researchers የተባለ አዲስ አሰራር የዘረጋ ሲሆን፣ ይህም ሳይንቲስቶች፣ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኢንጂነሮች የከፍተኛ ደረጃ AI ሞዴሎችን በነጻ እንዲጠቀሙ ዕድል ይሰጣል። አሰራሩ በመጀመሪያ ለ10,000 ተመራማሪዎች ክፍት የሚደረግ ሲሆን፣ እስከ 2027 ደግሞ ቁጥሩን ወደ 100,000 ለማሳደግ ታቅዷል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሎችን፣ የዳታ ሴኪዩሪቲ ጥበቃን፣ እስከ 4 ከሚደርሱ የቡድን አባላት ጋር አብሮ የመስራት ዕድልን እና የተለያዩ የስልጠና ድጋፎችን ያገኛሉ። ይህ እርምጃ ተመራማሪዎች በጽሁፍ እና በሰነድ ስራዎች የሚያባክኑትን ጊዜ በመቀነስ ትኩረታቸውን አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶች እና ምርምሮች ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል። @AddisIntelt.me/Addisintelligence/46551July 30, 2026 27