የገዛ ቤታችን ባይተዋር ሲያደርገን፡ በወሊሶ አብሬት ኑር መስጂድ የተፈፀመው የረቢዕ ዙልም!
===== ⨳ ===== ⨳ ===== ⨳ =====
"እንግዳ ተጠጋ ቢሉት፣ የቤቱን እቃ የት ላውጣው አለ" ይባላል በእኛ ሀገር። ልክ እስራኤላውያን የፍልስጤምን መሬት ተቆጣጥረው፣ ትክክለኛ ባለቤቶቹን በገዛ ቀያቸው ላይ በነፃነት መኖር እንደከለከሉና እንደሚያፈናቅሉት ሁሉ፤ ዛሬ በወሊሶ ከተማም ይህንኑ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ የሚያስታውስ ግፍ በሙሒቦች ላይ እየተፈፀመ ይገኛል። የአብሬት ሸይህ ሰይድ አበልራሙዝ ከኪሳቸው ገንዘብ አውጥተው በገዙት መሬት ላይ፣ ሙሪዶቻቸው ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘባቸውን አፍስሰው ያነፁትና አሳምረው የገነቡት "የአብሬት ሸህ ኑር መስጂድ" ዛሬ ለትክክለኛ ባለቤቶቹ ባዕድ ሆኗል።
የመፈናቀሉ ጅማሮ...
መጀመሪያ ነገሩ የተጀመረው "የኮሚቴ እና የተርቲብ ለውጥ" በሚል ስውር ሽፋን ነበር። ልክ እንደ ወራሪ ኃይል ቀስ በቀስ መስፋፋትን የመረጡት አዲሶቹ አካላት፣ "የተራዊህ ዚክር አቁሙ" በሚል ሰበብ የሱፊያውን ማህበረሰብ በማንገላታትና እስከ መደብደብ በሚደርስ በደል ብቸኛውን የመውሊድ ማክበሪያ መስጂዳቸውን ነጠቋቸው። ባለቤቶቹም ግጭትን በማስወገድ፣ ዋናውን ሰፊ መስጂድ ትተው በግቢው ውስጥ በምትገኝ አንዲት ጠባብ የመድረሳ ክፍል ውስጥ (ልክ እንደ ጋዛ ሰርጥ) ተጠቅጠው መውሊድን በከፍተኛ መከራና እንግልት ከአመት አመት ሲያከብሩ ቆዩ። ይህ በራሱ በገዛ ቤት ስደተኛ መሆን ነበር።
የዘንድሮው ክህደት እና ታላቁ መርዶ...
ዘንድሮ ግን ግፉ ጣሪያ ነካ! በመጅሊስ አስገዳጅነት አዲስ የኮሚቴ ለውጥ ሲደረግ፣ የመንግስት አካላት ባሉበት "መውሊድ በመስጂዱ ላይ መከበሩ አይቋረጥም፤ ሁሉንም እኩል እንመለከታለን" በማለት ቁርኣን ይዘው የማሉ አካላት፣ የገቡትን አማና በሉ። ያቺው ጠባብ የመድረሳ ክፍል እንኳ ተነፍጋ፣ አምና ያከበሩበት ቦታ ላይ ቆመው "በፍፁም በዚህ ግቢ ውስጥ አታከብሩም!" የሚል ጥብቅና አሳዛኝ ክልከላ ተጣለባቸው።
አባቶች መስርተው፣ አባባ ሙሪዶች አሳምረው በገነቡት ቤት የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ ማክበር መከልከል የዘንድሮው ረቢዕ ታላቅ መርዶ ነው።
የራስን መሬትና ንብረት ቀምቶ፣ ባለቤቱን "ውጣ" ከማለት በላይ ምን ዙልም አለ?
ፍትህ የጠማው ይህ ማህበረሰብ ድምፅ ይፈልጋል። የሚመለከታቸው የመንግስትም ሆነ የመጅሊስ አካላት ይህንን ግልፅ በደል በትኩረት ተመልክተው አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡ፣ ሁላችንም ይህን ግፍ ሼር በማድረግ የሙሪዶቹ ልሳን እንሁን!
#JusticeForAbretMurids #Woliso #Mawlid #StopTheInjustice
✍️በ yamin Amin















