ማስታወሻ፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) ፖርታል የመመዝገቢያ ሂደት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ UAT… — AAU Students Platform — TG.ME

#ማስታወሻ፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) ፖርታል የመመዝገቢያ ሂደት

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ UAT ፈተና ምዝገባ ነሐሴ 19 መጀመሩ ይታወቃል። በመሆኑም እንዴት መመዝገብ እንዳለባችሁ የሚከተለውን ደረጃ በደረጃ የተቀመጠ መመሪያ ተከተሉ፡

ምዝገባ ከመጀመራችሁ በፊት፡
Cost Sharing (በመንግስት ወጪ እንዲሸፈንላችሁ የምትፈልጉ)፡ ከቀበሌ ወይም ወላጆቻችሁ/ቤተሰቦቻችሁ ከሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ደብዳቤ አጻፉ (አዘጋጁ)።

ፋይዳ ቁጥር (Fayda Number)፡ ሁላችሁም የግዴታ የፋይዳ ቁጥር ሊኖራችሁ ይገባል።

የመመዝገቢያ ደረጃዎች (Step-by-Step Process)
ደረጃ 1፡ ፖርታሉን ክፈቱ (Open Portal)

ወደ AAU Admission Portal ይግቡ፡ https://admission.aau.edu.et

ደረጃ 2፡ ወደ Application ገጽ ሂዱ

ከላይ በስተግራ በኩል Undergraduate application የሚለውን ተጫኑ።

ከ Undergraduate Student ስር Apply የሚለውን ምረጡ።

Call for Undergraduate Regular Admission የሚለውን ተጫኑ።

የትምህርት ፕሮግራሞቹን ከተመለከታችሁ በኋላ Apply now የሚለውን ይጫኑ።

ደረጃ 3፡ Fayda ቁጥር ማረጋገጥ (FAYDA Validation)

የ FAYDA ቁጥራችሁን አስገቡ።

Validate የሚለውን ተጫኑ።

በስልካችሁ በ SMS የሚላክላችሁን OTP ቁጥር አስገቡ።

ደረጃ 4፡ አካውንት ክፈቱ (Create Account)

የሚሰራ የኢሜይል አድራሻ (Working email) ተጠቀሙ።

ቢያንስ 8 የፊደል/ቁጥር ርዝመት ያለው የይለፍ ቃል (Password) ፍጠሩ።

የመጀመሪያ አካውንት አፈጣጠሩን ከጨረሳችሁ በኋላ ሁልጊዜ በኢሜይላችሁና በፓስወርዳችሁ LOG IN እያደረጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።

ደረጃ 5፡ የትምህርት መረጃ መሙላት (Academic Profile)

"Your Academic Profile" የሚለውን ፎርም ትክክለኛ መረጃችሁን በመሙላት አጠናቅቁ።

UPDATE የሚለውን ከተጫናችሁ በኋላ NEXT የሚለውን ምረጡ።

ደረጃ 6፡ የመግቢያ ዓይነት መምረጥ (Admission Type)

በ Admission type ስር Regular የሚለውን ምረጡ።

ደረጃ 7፡ የትምህርት ክፍያ ዓይነት (Financing Your Study)

ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፡ Cost-sharing sponsorship (በመንግስት) ወይም Self-Sponsorship (በግል)።

ለ Cost-Sharing (በመንግስት ለሚሸፈን)፡

ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ቢያንስ አንዱን ተገቢ ምክንያት ምረጡ።

የተዘጋጀውን ማስረጃ በ PDF format (መጠናቸው ከ 5MB ያልበለጠ) አያይዙ (Attach አድርጉ)።

ደረጃ 8፡ የትምህርት ፕሮግራም ምርጫ (Program Choice)

Continue የሚለውን ተጫኑ።

Self-Sponsored (በግል) ከሆናችሁ፡ ከ Program Choice ፎርም ላይ 10 የትምህርት ምርጫዎችን ምረጡ።

ደረጃ 9፡ የFreshman ዘርፍ ምርጫ (ለ Cost-Sharing ብቻ)

ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፡ Natural Science Freshman ወይም Social Science Freshman።

ከዚያ Continue የሚለውን ተጫኑ።

ደረጃ 10፡ ሰነዶችን መስቀል (Upload Documents)

የሚከተሉትን ሰነዶች በ PDF format (እያንዳንዳቸው ከ 5MB ያልበለጠ) Upload አድርጉ፡

የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት (12th-grade result certificate)

ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት (9th-12th transcript)

ደረጃ 11፡ የፈተና ቦታ መምረጥ (Exam Location)

የ UAT ፈተና መፈተን የምትፈልጉበትን ቦታ ከ Drop-down አማራጮች ውስጥ ምረጡ።

ደረጃ 12፡ ስምምነት ማረጋገጥ (Consent)

የስምምነት ጽሑፉን (Consent Statements) አንብቡ።

Accept የሚለውን ምረጡ።

ከዚያ CONTINUE የሚለውን ተጫኑ።

ደረጃ 13፡ መረጃን መከለስ እና ማረጋገጥ (Review Application)

የሞላችሁትን መረጃ ለመከለስ View summary የሚለውን ተጫኑ።

ማስተካከል የምትፈልጉት ነገር ካለ ከላይ የሚገኘውን Academic Profile የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማስተካከል ትችላላችሁ።

ደረጃ 14፡ ክፍያ መፈጸም (Payment)

Continue to Payment የሚለውን ተጫኑ።

Proceed to Payment የሚለውን ምረጡ።

Completion of payment የሚለውን ተጫኑ።

750 ብር (ETB 750) በ Telebirr ይክፈሉ ወይም የተሰጠውን QR code Scan በማድረግ ክፍያውን ፈጽሙ።

ደረጃ 15፡ ከክፍያ በኋላ (After Payment)

የፈተና መግቢያ ቲኬት ለማውጣት UAT ADMISSION TICKET የሚለውን ተጫኑ።

የፈተና ፕሮግራም ለማየት EXAM SCHEDULE የሚለውን ተጫኑ።

የክፍያ መረጃ (Payment Information)
የምዝገባና የ UAT ፈተና ክፍያ፡ 750 ETB

የመክፈያ መንገድ፡ Telebirr ወይም QR Code Scan በማድረግ

ተጨማሪ ማስታወሻ፡ መግቢያ ፈተናውን የሚፈተኑት 25ሺ በላይ ተማሪዎች ሲሆኑ አልፈው የሚገቡት 5ሺ ብቻ ናቸው። ጊዜው ሳይሄድ ዛሬውኑ ተመዝግባችሁ ጥናት ጀምሩ።

#UAT #AAU #undergraduate #admission #exam

Share
@AAU_PLATFORM
❤4
August 31, 2026 1.2K 53