የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም 200 (ሁለት… — AAU Students Platform — TG.ME

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም 200 (ሁለት መቶ) ልዩ የፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጅቷል።

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ፣ የተቀመጡ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በብቃት የሚያልፉ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ዕድሉ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የ Presidential Scholarship Program ዕድሉ ተጠቃሚዎች፣ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ሰባት ኮሌጆች እና የሕግ ትምህርት ቤት ስር ባሉ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ይመደባሉ።

ነጻ የትምህርት ዕድሉ ሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል፣ መጠነኛ የኪስ ገንዘብ እና ከአጋር ተቋማት ጋር በሚኖር ትብብር ተጨማሪ ድጋፍና የስልጠና ዕድሎችን ያስገኛል፡፡

በዚህ የትምህርት ዕድል በወጥነት ተጠቃሚ ለመሆን፣ የዕድሉ ተጠቃሚዎች በየሴሚስተሩ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.50 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተመደቡበት የትምህርት ዘርፍ መቀጠል ይኖርባቸዋል።

የዚህ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች በቀጣይነት ዩኒቨርሲቲው የድኅረ-ምረቃ (Masters እና PhD) የትምህርት ዕድል ያገኛሉ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለፁ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://admission.aau.edu.et/UGAnnouncements

©tikvahuniversity

@AAU_PLATFORM
❤6
August 31, 2026 1K 24