ጊዜ ወስዳችሁ እረፉ!
እረፍት ስንፍና አይደለም፤ ሰውነትን፣ አእምሮንና መንፈስን ለማደስ የሚያስፈልግ ጤናማ ሂደት ነው።
1. እረፍት ኃይላችሁን ያድሳል
እረፍት ሰውነትና አእምሮ ከድካም እንዲያገግሙ ያደርጋል። ሁልጊዜ መስራት፣ መስጠት፣ መሮጥ … አንችልም፤ እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ማረፍና እንደገና መሙላት ያስፈልጋል።
2. እረፍት አእምሮን ያድሳል
ከሥራ፣ ከጭንቀትና ከችግሮች ለጥቂት ጊዜ መራቅ አእምሮን ያረጋጋል። ይህም በግልጽ ሁኔታ እንድናስብና ጥሩ ውሳኔ እንድንወስን ይረዳናል።
3. እረፍት ምርታማነትን ያሻሽላል
በቂ እረፍት ከወሰድን በኋላ በተሻለ ኃይል፣ ትኩረት፣ ፈጠራና ብቃት ወደ ሥራችን እንመለሳለን።
አስታውሱ! - እረፍት ከዓላማችን መመለስ አይደለም፤ ዓላማችንን ለመቀጠል ኃይልን እንደገና ማደስ ነው። ©Dr.eyob
🌥መልካም የእረፍት እሁድ!✴️
@AAU_PLATFORM

13
2
1August 30, 2026 1.8K 17