እግዚአብሔር ግን በጣም የዋህ ነው አይደል? በሚጠፋ ስብርባሪ ሳንቲም የማይጠፋ ትልቅ ሀብትን የሚሰጠን፤… — Unsaid thoughts💭 — TG.ME

እግዚአብሔር ግን በጣም የዋህ ነው አይደል?

በሚጠፋ ስብርባሪ ሳንቲም የማይጠፋ ትልቅ ሀብትን የሚሰጠን፤ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፈውን ዘላለም የሚያድለን፤ በተሰባሪ ጉልበት ለዘንታለም ብርታት የሚሆነን፤ ቁርስራሽ ፍርፋሪ ፣ የተቆጠበ ጊዜን ስንሰጠው ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቀውን እጅግ ውብ የሆነ፣ የማይያልፍና የማይጠፋ የመንግሥተ ሰማያትን የሚሸልመን!

ማን አለ ከእርሱ ውጭ በስፍር ሙሉ ሰጥቶ ቅንጥብጣቢ የሚለምን? አምላካችን በእውነት የዋህ ቸር አምላክ ነው! 🤍

@Un_said_thoughts
❤5
August 23, 2026 116 2